am_act_text_ulb/07/35.txt

1 line
766 B
Plaintext

\v 35 “በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ ያደረገህ ማን ነው?” ባሉት ጊዜ ተቀባይነትን ያሳጡት ይህ ሙሴ፦ እግዚአብሔር ገዥም ታዳጊም አድርጎ የላከው ነው። እግዚአብሔር ሙሴን በቊጥቋጦው ውስጥ በታየው መልአክ እጅ ላከው። \v 36 በግብፅና በቀይ ባሕር፣ በአርባ ዓመታቱ ወቅትም በምድረ በዳ ተአምራትንና ምልክቶችን ካደረገ በኋላ፣ ሙሴ ሕዝቡን ከግብፅ አወጣቸው። \v 37 ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል’ ብሎ ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው ያው ሙሴ ነው።