\v 33 ጌታም ለሙሴ እንዲህ አለው፤ ‘የቆምህበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ጫማህን አውልቅ። \v 34 በግብፅ ውስጥ ያሉትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፤ የሥቃይ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁና አሁን ና፤ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ።’