am_act_text_ulb/06/12.txt

1 line
736 B
Plaintext

\v 12 ሰዎቹን፣ ሽማግሌዎቹን፣ የሕግ መምህራኖቹንም አነሣሡ፤ እስጢፋኖስንም ይዘው ወደ ሸንጎው አቀረቡት። \v 13 እንዲህ ብለው የሚናገሩ ሐሰተኛ ምስክሮችንም አመጡ፤ “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን ተቃውሞ መናገርን አያቆምም። \v 14 ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዐትም ይለውጠዋል ሲል ሰምተነዋል።” \v 15 በሸንጎው ውስጥ የተቀመጡት ሁሉ አተኵረው ተመለከቱት፤ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት ሆኖ አዩት።