\v 38 አሁንም እነግራችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ፤ እነርሱንም ተዉአቸው፤ ይህ ዐሳብ ወይም ሥራ የሰዎች ከሆነ፣ ይጠፋል። \v 39 የእግዚአብሔር ከሆነ ግን፣ ልታጠፏቸው አትችሉም፤ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጋጩም እንኳ እንዳትገኙ።” እነርሱም በዐሳቡ ተስማሙ።