am_act_text_ulb/05/35.txt

1 line
736 B
Plaintext

\v 35 ከዚያም እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በእነዚህ ሰዎች ልታደርጉ ያሰባችሁትን በጥንቃቄ ተመልከቱት። \v 36 ከጥቂት ጊዜ በፊት ቴዎዳስ ትልቅ ሰው ነኝ በማለት ተነሥቶ ነበርና፤ አራት መቶ ያህል ወንዶችም ተከተሉት። እርሱ ተገደለ፤ ይታዘዙለት የነበሩትም ሁሉ ተበታትነው እንዳልነበሩ ሆኑ። \v 37 ከዚህም ሰው በኋላ፣ የገሊላው ይሁዳ በቈጠራው ቀናት ዐምፆ የተወሰኑ ሰዎችን አስከትሎ ሄደ። እርሱም ሞተ፤ እርሱን ይታዘዙት የነበሩትም ተበታተኑ።