am_act_text_ulb/05/26.txt

1 line
693 B
Plaintext

\v 26 ስለዚህ ሹሙ ከመኰንኖች ጋር ሄደ፤ መልሶም አመጣቸው፤ ያመጧቸው ግን በኀይል አልነበረም፤ ሕዝቡ በድንጋይ ይወግሯቸዋል ብለው ፈርተው ነበርና። \v 27 አምጥተዋቸው በነበረ ጊዜ፣ በሸንጎው ፊት አቆሟቸው። ሊቀ ካህናቱም ጠየቃቸው፤ \v 28 እንዲህም አላቸው፤ “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋታል፤ የዚህን ሰው ደም በእኛ ላይ ለማምጣትም ትፈልጋላችሁ።”