am_act_text_ulb/05/03.txt

1 line
824 B
Plaintext

\v 3 ጴጥሮስ ግን ሐናንያን እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፣ ለመንፈስ ቅዱስ እንድትዋሽና የመሬቱን ዋጋ ከፊል መጠን እንድታስቀር ሰይጣን ልብህን ለምን ሞላው? \v 4 መሬቱ ሳይሸጥ የአንተ እንደ ሆነ አይዘልቅም ነበርን? ከተሸጠ በኋላስ በአንተ ቊጥጥር ሥር አልነበረምን? በልብህ ይህን ነገር እንዴት ዐሰብህ? የዋሸኸው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰዎች አይደለም። \v 5 እነዚህን ቃሎች ሰምቶ፣ ሐናንያ ወደቀ፤ ሞተም። በሰሙት ሁሉ ላይም ታላቅ ፍርሀት መጣ። \v 6 ጐበዛዝቱ ወደ ፊት መጡና ከፈኑት፤ ወደ ውጭ አውጥተውም ቀበሩት።