\v 19 ነገር ግን ጴጥሮስና ዮሐንስ መልሰው እንዲህ አሏቸው፤ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ እናንተን መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል እንደ ሆነ እናንተ ፍረዱ። \v 20 እኛ ስላየናቸውና ስለ ሰማናቸው ነገሮች ለመናገር ዝም ማለት አንችልም።”