am_act_text_ulb/03/24.txt

1 line
640 B
Plaintext

\v 24 አዎ፣ ከሳሙኤል ጀምሮና ከእርሱም በኋላ የተናገሩ ነቢያት ሁሉ ስለ እነዚህ ቀኖች ተናግረዋል። \v 25 እናንተ የነቢያትና ‘በዘርህ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ’ ብሎ ለአብርሃም እንደ ተናገረው፣ ከአባቶቻችሁ ጋር እግዚአብሔር ያደረገው ኪዳን ልጆች ናችሁ። \v 26 እግዚአብሔር አገልጋዩን ካስነሣ በኋላ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ መልሶ ሊባርካችሁ ነው።