am_act_text_ulb/03/01.txt

1 line
609 B
Plaintext

\c 3 \v 1 ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ፣ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ ነበር። \v 2 ወደ ቤተ መቅደሱ ከሚገቡ ሰዎች ምጽዋት መለመን እንዲችል፣ ውብ ተብሎ በሚጠራው በቤተ መቅደሱ በር ላይ ሰዎች በየቀኑ በሸክም አምጥተው የሚያስቀምጡት፣ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ዐንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። \v 3 ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ቤተ መቅደሱ ሊገቡ ሲሉ ባያቸው ጊዜ፣ ምጽዋት ለመነ።