am_act_text_ulb/02/01.txt

1 line
589 B
Plaintext

\c 2 \v 1 በበዓለ ኀምሳ ቀን ሁሉም በአንድነት አንድ ስፍራ ላይ ነበሩ። \v 2 ድንገት እንደ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ ተቀምጠውበት የነበረውን ቤትም ሞላው። \v 3 እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳናት ታዩአቸው፤ በእያንዳንዳቸው ላይም ተቀመጡባቸው። \v 4 ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ እንደ ሰጣቸውም በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።