am_act_text_ulb/01/09.txt

1 line
665 B
Plaintext

\v 9 ጌታ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ሐዋርያቱ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረው። \v 10 ትኵር አድርገው ወደ ሰማይ እየተመለከቱ ሳለ፣ ድንገት ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ። \v 11 እነርሱም፣ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን እዚህ ትቆማላችሁ? ወደ ሰማይ የወጣው ይህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁበት ሁኔታ ተመልሶ ይመጣል” አሏቸው።