\v 23 ስለ ሆነም በማግስቱ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ሥነ ሥርዓት ከወታደራዊ መኮንኖችና ከከተማዋ ታዋቂ ሰዎች ጋር ወደ አዳራሹ ገቡ። ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን ወደ እነርሱ አመጡት። \v 24 ፊስጦስም እንዲህ አለ፤ “ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ እዚህ ከዚህ ከእኛ ጋር ያላችሁም ሰዎች ሁሉ፣ ይህን ሰው ተመልከቱት፤ በኢየሩሳሌም እዚህም ደግሞ ያሉት የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ከእኔ ጋር ተማከሩ፤ ከእንግዲህ ወዲያ በሕይወት መኖር የለበትም ብለውም ጮኹብኝ።