\v 14 ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎችም ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ጳውሎስን እስከምንገድል ድረስ፣ እኽል እንዳንቀምስ በታላቅ ርግማን ተማምለናል። \v 15 ስለዚህ አሁን ጳውሎስን ወደ አንተ እንዲያወርደውና አንተ የእርሱን ጉዳይ ይበልጥ በትክክል እንደምታይለት አስመስለህ ፣ ሸንጎው ለሻለቃው ያመልክት። በእኛ በኩል ግን እዚህ ከመምጣቱ በፊትም ቢሆን ልንገድለው ዝግጁ ነን።”