\v 4 ጴጥሮስ ዐይኖቹን ምጽዋት በሚለምነው ሰውዬ ላይ በማድረግ፣ ከዮሐንስ ጋር “ወደ እኛ ተመልከት” አለው። \v 5 ዐንካሳውም፣ ከእነርሱ አንድ ነገር ለመቀበል በመጠበቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ። \v 6 ጴጥሮስ ግን፣ “ብርና ወርቅ የለኝም፣ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ። በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተራመድ” አለው።