\v 21 በዚያም ከተማ ወንጌልን ሰብከው ብዙ ደቀ መዛሙርትን ካፈሩ በኃላ፣ ወደ ሊስጥራ ፣ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ። \v 22 የደቀመዛሙርቱንም ልብ እያበረቱ በእምነት እንዲጸኑ መከሯቸው።ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ውስጥ ማለፍ እንዳለብንም ነገሯቸው።