\c 14 \v 1 በኢቆንዮንም እንዲህ ሆነ ፤ ጳውሎስና በርናባስ ወደ አይሁድ ምኵራብ አብረው ገብተው፣ ከአይሁድና ከግሪክ ብዙ ሰዎች እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ። \v 2 ነገር ግን ማመን ያልፈለጉ አይሁድ የአሕዛብን ልብ በመቀስቀስ በወንድሞች ላይ በክፋት አነሣሡአቸው።