\v 30 ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝቡም በአንድነት ተሰባስበው ጳውሎስን ያዙት፤ ጎትተውም ከቤተ መቅደስ አስወጡት፤ በሮቹም ወዲያው ተዘጉ። \v 31 ሊገድሉት ሲሞክሩም፣ “ኢየሩሳሌም ሁሉ እጅግ ታውካለች” የሚል ወሬ ወደ ጭፍሮቹ አለቃ ደረሰ።