\v 6 \v 7 \v 8 6 ሐዋርያት በአንድነት ተሰብስበው ሳለ “ጌታ ሆይ፣ ይህ የእስራኤልን መንግሥት የምትመልስበት ጊዜ ነውን?” ብለው ጠየቁት። 7 እርሱም እንደዚህ አላቸው፤ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ጊዜ ወይም ወቅት ማወቅ እናንተን አይመለከትም። 8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ሲመጣ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮች ትሆናላችሁ።”