\v 11 ከሦስት ወር በኋላ አፍንጫው ላይ የመንታ ወንድማማች ዓርማ በነበረበት ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈ የእስክንድርያ መርከብ ላይ ተሳፍረን ጕዞ ጀመርን። \v 12 ወደ ሲራኩስ ከተማ ከደረስን በኋላም እዚያ ሦስት ቀን ቆየን።