\v 34 በመካከላቸው ችግረኛ ሰው አልነበረም፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ ሽጠው የሽያጩን ገንዘብ ያመጡትና፣ \v 35 በሐዋርያት እግር አጠገብ ያስቀምጡት ነበርና። አከፋፈሉም ይደረግ የነበረው እያንዳንዱ አማኝ በሚያስፈልገው መሠረት ነው።