\v 30 ከዚያም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው። \v 31 ደብዳቤውንም አንብበው ስለ ተጽናኑ በጣም ደስ አላቸው። \v 32 ደግሞም ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ስለ ነበሩ፣ወንድሞችን በብዙ ቃል በመምከር አበረታቱአቸው።