\v 5 ጴጥሮስም በወኅኒው ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ጉባኤው ወደ እግዚአብሔር አጥብቆ ይጸልይ ነበር። \v 6 ሄሮድስ ሊያወጣው ባሰበበት በዚያ ሌሊት፣ ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለቶች ታስሮ በሩን በሚጠብቁ ሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር።