\v 5 ሳውልም፣ "ጌታ ሆይ፣ ማን ነህ?" ብሎ መለሰ፤ ጌታም፣ “አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ፤ \v 6 ነገር ግን ተነሥተህ ወደ ከተማው ግባ፤ ማድረግ ያለብህም ይነገርሃል” አለ። \v 7 ከዚያም ከሳውል ጋር የተጓዙት ሰዎች ድምፁን እየሰሙ፣ ማንንም ግን ሳያዩና ሳይነጋገሩ ቆሙ።