\v 3 ይህ አይሁድን ደስ እንዳሰኛቸው ካየ በኋላ ጴጥሮስንም ያዘው። ይህ የሆነው በቂጣ በዓል ጊዜ ነበር። \v 4 ከያዘውም በኋላ ወደ ወኅኒ አገባው፤ እንዲጠብቁትም እያንዳንዳቸው አራት ወታደሮች ያሏቸው ቡድኖችን መደበ፤ ከፋሲካ በኋላ ወደ ሕዝቡ ሊያቀርበው ዐስቦ ነበር።