\v 13 የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ፣ የአባቶቻችን አምላክ አገልጋዩን ኢየሱስን አክብሮታል። እርሱ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትና ጲላጦስ ሊፈታው ወስኖ ሳለ፣ በፊቱ የካዳችሁት ነው። \v 14 ቅዱሱንና ጻድቁን ካዳችሁት፤ በእርሱም ፈንታ ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ።