\v 22 ከወጣትነት ምኞት ራቅ፣ በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን ተከታተል፡፡ \v 23 ነገር ግን ጠብን እንደሚያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፡፡