am_2th_text_ulb/03/10.txt

1 line
621 B
Plaintext

\v 10 ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ሊሠራ የማይወድ ማንም ቢኖር እርሱ መብላት የለበትም” ብለን አዝዘናችሁ ነበር። \v 11 በመካከላችሁ ሥራ ፈት ሆነው የሚመላለሱ አንዳንዶች መኖራቸውን ሰምተናልና፤ ሥራ አይሠሩም ነገር ግን በሰው ጉዳይ ጣልቃ ይገባሉ። \v 12 እንደነዚህ ያሉትን በጸጥታ እንዲሠሩና የራሳቸውን ምግብ እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸዋለንም።