am_2th_text_ulb/03/06.txt

1 line
856 B
Plaintext

\v 6 ወንድሞች ሆይ፣ ከእኛ እንደተቀበላችሁት ልማድ ሳይሆን ሥራ በመፍታት ከሚኖር ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። \v 7 እንዴት ምሳሌነታችንን መከተል እንደሚኖርባችሁ እናንተው ታውቃላችሁ። በመካከላችሁ በስንፍና አልተመላለስንም፣ \v 8 ወይም ገንዘብ ሳንከፍል የማንንም ምግብ አልበላንም። ከዚያ ይልቅ ከእናንተ በማንም ላይ ሸክም ላለመሆን በድካምና በጥረት ሌሊትና ቀን ሠራን። \v 9 ይህንን ያደረግነው እኛን ትመስሉ ዘንድ ምሳሌ ልንሆንላችሁ ብለን እንጂ ሥልጣን ስላልነበረን አይደለም።