am_2pe_text_ulb/02/12.txt

1 line
783 B
Plaintext

\v 12 እነዚህ አእምሮ እንደ ጎደላቸው እንስሳት ለምርኮና ለጥፋት የተፈጠሩ ናቸው፤ የሚሳደቡትን ስለማያውቁ ይጠፋሉ። \v 13 እነርሱ የዐመፃቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ በቀን በመስከርና ያለ ልክ በመፈንጠዝ ይኖራሉ ፤ እነርሱ አሳፋሪዎችና ነውረኞች ናቸው። ከእናንተ ጋር ግብዣ ላይ ሲገኙ፣ በአታላይ ፈንጠዝያቸው ሐሴት ያደርጋሉ። \v 14 ዐይናቸው ቅንዝር የተሞላ በመሆኑ ኀጢአትን ከመሥራት ከቶ አይቈጠቡም፤ ጽኑ ያልሆኑትን ሰዎች ያስታሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ልጆች ናቸው።