am_2pe_text_ulb/02/07.txt

1 line
585 B
Plaintext

\v 7 በሕገ ወጦች ሴሰኝነት ነፍሱ እየተጨነቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን ግን አዳነው፤ \v 8 ያ ጻድቅ ሰው በመካከላቸው ሲኖር በየቀኑ ያየውና ይሰማው በነበረው ሕገ ወጥ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱ ትጨነቅ ነበር። \v 9 ጌታ፣ እግዚአብሔርን የሚመስሉትን ሰዎች ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።