am_2co_text_ulb/07/08.txt

1 line
721 B
Plaintext

ምናልባት እንኳ በመልዕክቴ አሳዝኜያችሁ ቢሆን፥ምንም እንኳ እንዳዘናችሁ ሳይ ለጥቂት ጊዜ እኔም አዝኜ ቢሆንም፣አልፀፀትም፤ አሁን ደግሞ እደሰታለሁ፤የምደሰተውም ስላዘናችሁ ሳይሆን ሃዘናችሁ ንስሃን ስላደረገላችሁ ነው። እግዚአብሔር የሚወደው አይነት ሃዘን እየተለማመዳችሁ ስለሆነ በእኛ ምክንያት ኪሳራ ውስጥ አልገባችሁም። እግዚአብሔር የሚወደው ሃዘን ያለ ፀፀት የሆን ድነትን የሚፈፅም ንስሃ ያመጣል፥ዓለማዊ ሃዘን ግን ሞትን ያመጣል።