am_2co_text_ulb/05/01.txt

1 line
460 B
Plaintext

ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈራርስ እንኳ በሰማይ በሰው እጆች ያልተሰራ ዘላለማዊ ቤት ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደተሰራልን እናውቃለን። በዚህ ድንኳን ውስጥ ሆነን እንቃትታለን፥ሰማያዊ መኖርያችንንም ልንለብስ እንናፍቃለን፤ ምክንያቱም ያን ስንለብስ ራቁታችንን ሆነን አንገኝምና ነው።