am_2co_text_ulb/01/05.txt

1 line
711 B
Plaintext

የክርስቶስ መከራ ስለእኛ እንደበዛ ፥መፅናናታችንም በክርስቶስ በኩል እንዲሁ ይበዛልናል። ነገር ግን መከራን ብንቀበል፥ስለናንተ መፅናናት እና ድነት ነው። ወይንም ደግሞ የእኛ መፅናናት የእናንተም መፅናናት ማለት ነው፤ይህም እኛ በምንቀበለው መከራ እናንተም በተመሳሳይ መልኩ በትእግስት አብራችሁን ስለምትካፈሉ ነው። ስለናንተም ያለን መታመን ፅኑ ነው፥መከራችንን እንደምትካፈሉ ሁሉ መፅናናታችንን ደግሞ እንድትካፈሉ እናውቃለን።