am_2co_text_ulb/04/01.txt

1 line
522 B
Plaintext

እንግዲህ፥ይህ አገልግሎት ስላለን እንዲሁም ምህረት ስለተቀበልን፥ ተስፋ አንቆርጥም። በዚያ ፈንታ ግን አሳፋሪ እና ድብቅ የሆኑ መንገዶችን ክደናል። የተንኮል ህይወት አንኖርም፥የእግዚአብሔርንም ቃል ያለ አግባብ አንይዝም። እውነትንም እየተናገርን ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት ለእያንዳንዱ ሰው ህሊና እናቀርባለን።