am_2co_text_ulb/06/14.txt

1 line
794 B
Plaintext

\v 14 ከማያምኑ ጋር በማይሆን መንገድ በአንድ ላይ አትተሳሰሩ። ፅድቅ ከአመፀኝነት ጋር ምን መዛመድ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለው? \v 15 ክርስቶስስ ከቤልዖር ጋር ምን ስምምነት አለው? የሚያምንስ ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው? \v 16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስስ ከጣዖታት ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔር "ከእነርሱም ጋር አድራለሁ፥በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፥ እነርሱም ህዝብ ይሆኑኛል" ብሎ ስለተናገረ እኛ የህያው እግዚአብሔር መቅደሶች ነን።