am_2co_text_ulb/01/08.txt

1 line
653 B
Plaintext

ወንድሞች ሆይ፥በእስያ ስለደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ወደፊት በህይወት ለመኖር ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከአቅማችን በላይ ከብዶን ነበር። በርግጥም ሞት ተፈርዶብን ነበር። ሆኖም ግን ያ የደረሰብን መከራ ሙታንን በሚያነሳ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን አደረገን። እርሱ ከብርቱ ጥፋት አዳነን እንዲሁም ያድነናል። መታመናችንን በእርሱ ላይ አድርገናል፤እርሱም ይታደገናል።