\v 7 እንግዲህ እናንተ ክፉ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፥ ይህንም የምናደርገው ፈተናውን ያለፍን መሰለን ለመታየት አይደለም፥ ነገር ግን ፈተናውን ያላለፍን ብንመስልም እንኳ፣ እናንተ ትክክል የሆነውን ታደርጉ ዘንድ እጸልያለው። \v 8 ስለ እውነት እንጂ የእውነት ተቃራኒ የሆነ ነገር መሥራት አንችልምና።