am_2co_text_ulb/11/07.txt

1 line
705 B
Plaintext

\v 7 የእግዚአብሔርን ወንጌል በነፃ ስለሰበኩለችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትሉ እኔ ራሴን በማዋረዴ ኋጢያት ሰራሁን? \v 8 እናንተን ማገልገል እችል ዘንድ ከእነርሱ እርዳታ በመቀበል ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት«ጎዳሁ»። \v 9 አብሬአችሁ በሆንኩና በተቸገርሁ ጊዜም በማንም ላይ ሸክም አልሆንሁም። ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የሚያስፈልገኝን ሰጥተዋልና። በሁሉም ረገድ ለእናንተ ሸክም ከመሆን ተጠንቅቄአለሁ፣ይህን ማድረጌንም እቀጥላለው ።