am_2co_text_ulb/01/12.txt

1 line
801 B
Plaintext

\v 12 የምንመካው በህሊናችን ምስክርነት ላይ ነው። ምክንያቱም በዚህ ዓለም ስንመላለስ የነበረው በንፁህ ህሊና እና ከእግዚአብሔር በሚሰጥ ቅንነት ነበር። በተለይም ከናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት የተመሰረተው በእግዚአብሔር ፀጋ ላይ እንጂ በምድራዊ ጥበብ ላይ አልነበረም። \v 13 ልታነቡትና ልትረዱት የማትችሉትን አንዳችም ነገር አንዳልፃፍንላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ \v 14 እናንተም በከፊል እንደተረዳችሁን በጌታችን በኢየሱስ ቀን እናንተ በእኛ እንደምትመኩ እኛም እንዲሁ በእናንተ እንመካለን።