Mon Jul 02 2018 12:18:34 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
kaleab 2018-07-02 12:18:34 +03:00
parent a61ec6fa1a
commit 1086b53671
4 changed files with 12 additions and 1 deletions

2
14/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 7 አሳ ለይሁዳ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ዙሪያቸውን ግንቦችና፣ የብረት አጥር ያላቸው የመጠበቂያ ማማዎችን በመሥራት እነዚህን ከተሞች እንጠብቅ፡፡ አምላካችን ያህዌ እንዲረዳን ስለ ለመንነው ይህች አገር የእኛ ሆናለች፡፡ እንዲረዳን ለመንነው፤ እርሱም በአገራችን ሁሉ ሰላም ሰጠን፡፡›› ስለዚህ ግንቦች ሠሩ፤ ሥራውም ተከናወነላቸው፡፡
\v 8 አሳ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ወታደሮች ነበሩት፡፡ ሁሉም ትልልቅ ጋሻዎችና ጦሮች ይይዙ ነበር፤ ከብንያም ሰዎች ሁለት መቶ ሰማንያ ሺ ወታደሮችም ነበሩ፡፡ እነርሱም ጋሻዎች፣ ቀስቶችና ፍላጻዎች ይይዙ ነበር፡፡

3
14/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 9 ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚሊዮን ወታደሮችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ይሁዳን ወረረ፡፡ ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ እስካለው እስከ መሪሳ ድረስ መጣ፡፡
\v 10 አሳ ሊገጥመው ወጣ፤ ሁለቱም ሰራዊቶች በጽፋታ ሸለቆ ቦታቸውን ያዙ፡፡
\v 11 በዚህ ጊዜ አሳ እንዲህ በማለት ወደ አምላኩ ወደ ያህዌ ጮኸ፤ ‹‹ያህዌ ሆይ፣ ብዛት ያለውን ሰራዊት መቋቋም እንዲችሉ ደካሞችን የሚረዳ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ ይህን ግዙፍ ሰራዊት ለመግጠም መጥተናል፤ ያህዌ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህ፤ ሰውም አያሸንፍ፡፡››

4
14/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,4 @@
\v 12 ከዚያም የኢትዮጵያውያንን ሰራዊት ድል እንዲያደረርጉ ያህዌ አሳንና የይሁዳን ሰዎች ረዳቸው፡፡ እነርሱም ሸሹ፤
\v 13 አሳና ሰራዊቱም በደቡብ ምዕራብ እስካለው እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዷቸው፡፡ ብዛት ያላቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ፤ በሕይወት ያሉትም ጨርሶ መዋጋት አልቻሉም፡፡ በያህዌና በሰራዊቱ ጨርሶ ድል ሆኑ፤ የይሁዳም ሰዎች እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፡፡
\v 14 በዚያ የነበሩትን ሰዎች ያህዌ አሸብሯቸውና ምንም እንዳይዋጉ አድርጓቸው ስለ ነበር፤ የይሁዳ ሰዎች በጌራራ አካባቢ የነበረውን ከተማ መደምሰስ ቻሉ፡፡ የይሁዳ ሰራዊት ከመንደሮቹ ዋጋ ያለውን ነገር ሁሉ ወሰደ፡፡
\v 15 ከብቶቻቸውን እየጠበቁ በድንኳን የነበሩ የአገሬውን ሰዎች አጠቁ፤ ብዛት ያላቸው በጐችና ፍየሎች፣ እንዲሁም ግመሎች ወስደው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡

View File

@ -164,6 +164,8 @@
"13-16",
"14-title",
"14-01",
"14-05"
"14-05",
"14-07",
"14-09"
]
}