am_1ti_text_ulb/06/15.txt

1 line
505 B
Plaintext

\v 15 እርሱም መገለጡን የተባረከውና፣ ብቻውን ኃያል የሆነው፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ በወሰነው በትክክለኛው ጊዜ ያሳያል፡፡ \v 16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፡፡ ማንም ሰው አላየውም ሊያየውም አይችልም፡፡ ለእርሱ ክብር የዘላለምም ኃይል ይሁን፡፡ አሜን፡፡