am_1ti_text_ulb/04/06.txt

1 line
697 B
Plaintext

\v 6 እነዚህን ነገሮች ለወንድሞች ብታስረዳ፣ በእምነት ቃሎች እና በተከተልከውም መልካም ትምህርት የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ፡፡ \v 7 ራስህን እግዚአብሔርን ለመምሰል አሰልጥን እንጂ፣ አሮጊቶች የሚወዱአቸውን አለማዊ ተረቶችን አትቀበል፡፡ \v 8 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጥቂት ነገር ይጠቅማል፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን መምሰል ለአሁኑና ለሚመጣውም ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል፡፡