am_1ti_text_ulb/02/01.txt

1 line
629 B
Plaintext

\c 2 \v 1 ስለዚህ ከሁሉ በፊት፣ ጸሎት፣ ምልጃና ምሥጋና ስለ ሰዎቸ ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር፣ \v 2 በጸጥታ ሕይወት ሰላማዊ ኑሮ እንድንኖር፣ ለነገሥታትና በሥልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ፡፡ \v 3 ይህም በአዳኛችን በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ተቀባይነት ያለው ነገር ነው፡፡ \v 4 እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ሁሉ ወደ ማውቅ እንዲደርሱ ይፈልጋልና፡፡