am_1ti_text_ulb/01/15.txt

1 line
832 B
Plaintext

\v 15 ‹‹ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣ›› የሚለው መልዕክት ሁሉም ሊቀበሉት የተገባና አስተማማኝ ነው፡፡ እኔም ከእነዚህ ሁሉ የባስኩ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡ \v 16 በዚህም ምክንያት ከኃጢአተኞች ዋነኛ በምሆን በእኔ ክርስቶስ ኢየሱስ ትእግስቱን ሁሉ ሊያሳይ ምሕረትን አገኘሁ፤ ይህም የሆነው በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለም ሕይወት ለሚያገኙ ምሳሌ እሆን ዘንድ ነው፡፡ \v 17 ስለዚህ ለዘላለም ንጉሥ ፣ ለማይሞተው እና ለማይታየው፣ ብቻውን አምላክ ለሆነው፣ ክብርና ግርማ ለዘላለም ይሁን፡፡ አሜን፡፡