am_1th_text_ulb/05/12.txt

1 line
677 B
Plaintext

\v 12 ወንድሞች ሆይ፣በመካከላችሁ በማገልገል የሚለፉትንና በጌታ የሚያስተዳድሯችሁን፣ የሚመክሯችሁንም እንድታከብሯቸው እንጠይቃችኋለን። \v 13 ደግሞም በሥራቸው ምክንያት ከፍ ያለ የፍቅር አክብሮት እንድታሳዩአቸው እንጠይቃችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ኑሩ። \v 14 ወንድሞች ሆይ እንመክራችኋለን፣ ያለ ሥርዓት የሚመላለሱትን ገስጹአቸው፣ ድፍረት ያጡትን አበረታቱአቸው፣ ደካሞችን ደግፉአቸው፣ሰውን ሁሉ ታገሱ።