am_1th_text_ulb/04/09.txt

1 line
874 B
Plaintext

\v 9 የወንድማማች መዋደድን በተመለከተ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፣ እርስ በርስ ስለመዋደድ እናንተው ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና። \v 10 በመቄዶንያ ላሉ ወንድሞች ሁሉ ይህንን ታደርጋላችሁ፣ ይሁን እንጂ ወንድሞች ሆይ፣ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉት ደግሞ እንመክራችኋለን። \v 11 ደግሞም ልክ እንዳዘዝናችሁ በጸጥታ እንድትኖሩ፣ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩና በገዛ እጆቻችሁ እንድትሠሩ እንመክራችኋለን። \v 12 በማያምኑት ዘንድ በአግባብ እንድትመላለሱና በኑሮአችሁ ምንም የሚጎድላችሁ እንዳይኖር ይህንን አድርጉ።