am_1th_text_ulb/02/17.txt

1 line
778 B
Plaintext

\v 17 ወንድሞች ሆይ፣ እኛ ለጥቂት ጊዜ በልባችን ሳይሆን በአካል ተለይተናችሁ ነበር፣ በመሆኑም በነበረን ታላቅ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት የተቻለንን ያህል ጥረት አድርገናል፣ \v 18 ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልገን ነበር፣ እኔ ጳውሎስም ከአንድም ሁለት ጊዜ ሞከርኩኝ፣ ነገር ግን ሰይጣን አዘገየን። \v 19 ጌታችን ኢየሱስ በሚመጣበት ጊዜ በፊቱ ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም የመክበራችን አክሊል እንደሌሎቹ ሁሉ እናንተ አይደላችሁምን? \v 20 ምክንያቱም እናንተ ክብራችንና ደስታችን ናችሁ።