am_1th_text_ulb/02/14.txt

1 line
805 B
Plaintext

\v 14 እናንተም ወንድሞች ሆይ፣ በይሁዳ የሚኖሩ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑትን የእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት የምትመስሉ ሆናችኋል፣ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደደረሰባቸው እናንተ ደግሞ ከገዛ ራሳችሁ ሕዝብ ያንኑ መከራ ተቀብላችኋልና፣ \v 15 አይሁድ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ገደሉ፣ እኛንም አሳደዱን፣ እነርሱ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኙትም፥ ሰውን ሁሉ ይቃወማሉ። \v 16 ዘወትር ኀጢአታቸውን ለማብዛትም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ይከለክሉናል። ቁጣው በላያቸው ላይ መጥቶባቸዋል።