am_1th_text_ulb/02/07.txt

1 line
705 B
Plaintext

\v 7 ይልቁንም እናት የራስዋን ልጆች እንደምትንከባከብ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን። \v 8 ለእናንተ ካለን ፍቅር የተነሳ የእግዚአብሔርን ወንጌል ብቻ ሳይሆን የራሳችንን ሕይወት እንኳን ጨምረን ብንካፈላችሁ ደስ ይለን ነበር፣ ምክንያቱም ለእኛ እጅግ የተወደዳችሁ ሆናችኋልና። \v 9 ወንድሞች ሆይ! የእግዚአብሔርን ወንጌል በሰበክንላችሁ ጊዜ በማናችሁም ላይ ሸክም ላለመሆን ቀንና ሌሊት እንደሠራን ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሳላችሁ።